ስለ ሥነ ጥበቡ
ይዘቱን፣ ምልዕቱን እና ማስታወሻዎችን ስለ መልቀቁ።
የአርማው ትርጉም
አርማው የ "ተላሶን" ሁሉንም ፊደላት የያዘ ሲሆን የተላሶን ምልክትም ለሙዚቃ ያለውን ፍቅር በኤም (M) ፊደል ይገልጻል። የአንድ መስመር ንድፉ እና አንዱ መስመር በሌላው ላይ መደገፉ ሰዎች በተለይም ኢትዮጵያውያን እንዴት እርስ በእርስ ተደጋግፈው እንዳሉ ያሳያል። ሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች በአንድነት የተሳሰሩ ናቸው፣ እኛ ተጋብተናል፣ ተዋልደናል። እኛ አንድ ነን የሚለውን አስተሳሰብ እሱ ተላሶን ከምልክቱ ጋር ሊያስገነዝቡን ያሉ ናቸው። እንዲሁም የሙዚቃ ኖታንም ይመስላል፣ በርግጥ ይሄን የሚመስል ኖታም የለም - ምክንያቱም ይህን ስሜት እንዲሰጥ ተደርጎ ስላልተነደፈ ነው። አርማው ሊያሳየን የሚሞክረው ተላሶን ራሱ አዲሱ የሙዚቃ ኖታ እንደሆነ ነው። ብዙ የአርማ ንድፎችን የሞከርን ሲሆን ዲጂታላዊ ለማድረግም ፈልገን ነበር፣ ነገር ግን በኔ እጅ የተሰራሁት ንድፍ ውብና ማራኪ በመሆኑ እንዲጸና ሆኗል።
መነሻ ሃሳቦች
ከሚኒሊክ እና ከቴዎድሮስ ስዕሎች እና ምስክሮች የተወሰዱ ናቸው።
የፊደል ገበታ እና ንድፎች
ምን አይነት የፊደል ቅርጽ መጠቀም እንዳለብን አሁንም እየሞከርን ነው፣ እንዲሁም የራሳችንን የተላሶን ፊደል ለመፍጠር እያሰብን ነው። ነገር ግን ለጊዜው በሶስት የተለያዩ የፊደል አይነቶች ላይ ሙከራ እያደረግን ነው።

የዘፈኑ ሽፋን ንድፍ
ሽፋኑ ቴዎድሮስ ሚኒሊክን ንጉሳዊ አስተዳደርን ሊያስተምረው ወደ ግዛቱ የወሰደበትን ጊዜ ለማሳየት የሚያገለግል ነው። ቴዎድሮስ ሚኒሊክን ይዞ ወደ ፋሲለደስ ግንብ ሲያመራ ያሳያል። አንዳንዶቹን ገጽታዎች ለማግኘት AI የተጠቀምን ቢሆንም ሽፋኑን በመስራት እና በተደጋጋሚ በማረም ከ 2 እስከ 3 ሳምንታት ወስዶብናል። በጣም ረጅም ጊዜ ከመውሰዱ የተነሳ በእርሳስ ሌላ አይነት ገለጻ ልሰጠው ሁሉ አስቤ ነበር። በእርግጥም አድሰነዋል AI የሰጠንን ንድፍ ቀጥታ አልተጠቀምንም። ምንም እንኳን ንድፉ ከዘፈኑ ጋር የተያያዙ ብዙ ነገሮች ቢኖሩትም፣ ተላሶን ለሙዚቃው ዶክመንተሪ ይፋ ሊያደርግ ስለሆነ፡ ብዙ የተደበቁ ምስጢራት ስላሉት አሁን ምንም አይነት ፍንጭ መስጠት አልፈለኩም። በርካታ የሽፋን ንድፎችንም ሞክረናል በመጨረሻም ልባችን ያረፈው ግን በዚህ ንድፍ ላይ ነው።









