ስለ እኔ

በቴክኖሎጂ፣ ባህል እና ፈጠራ በዓለም ላይ ለውጥ ለማምጣት የቆረጥኩ ግለሰብ ነኝ።

ተልእኮየ

ንግዶችን እና ግለሰቦችን በፈጠራ ቴክኖሎጂ እና ዲዛይን ማጎልበት።

ራዕየ

በምንነካው እያንዳንዱ ፕሮጀክት ላይ አዎንታዊ ለውጥ እና እድገትን በማምጣት በዲጂታል ለውጥ ውስጥ ግንባር ቀደም መሆን።

ምን ያተጋኛል?

የስራዬ እምብርት ተግባሮቼን እና ውሳኔዎቼን የሚመሩ እሴቶች ናቸው። እነዚህ መርሆች ስራዬን ይቀርፃሉ እና ማን እንደሆንኩ ይገልፃሉ።

እርስዎ ይቀድማሉ

በምሰራው ነገር ሁሉ ለደንበኞቼ ፍላጎት ቅድሚያ እሰጣለሁ።

ትክክለኛውን ነገር ማድረግ

ራሴን በከፍተኛ የሥነ ምግባር ደረጃዎች እመራለሁ።

ትብብር ተአምር ይፈጥራል

የጋራ ግቦችን ለማሳካት ከደንበኞቼ ጋር በቅርበት እሰራለሁ።

ሁልጊዜም ከሚጠበቀው በላይ መሥራት

በእያንዳንዱ ተግባር የላቀ ጥራትን ለማቅረብ እንተጋለን።

በተለየ መንገድ ማሰብ

እድገትን ለማምጣት አዳዲስ ሀሳቦችን እንተገብራለን።

እኔ እንደተገለጠ መጽሐፍ ነኝ

ከደንበኞቻችን ጋር መተማመንን ለመገንባትና ለማጽናት በግልጽ እሰራለሁ።

ስህተቶቻችንን እናርማለን

ለድርጊቶቻችን ሃላፊነት እንወስዳለን።

ሁሉም ሰው ዋጋ አለው

የተለያዩ አመለካከቶችን እናከብራለን እና ሁሉንም ሰው በፍትሃዊነት እንይዛለን።

እኔን ይተዋወቁ

ለምርትዎ ለውጥ የሚያመጡ አዳዲስ የሆኑ መፍትሄዎችን በመፍጠር አላማ የምሰራ ግለሰብ ነኝ።

HF

ሃብተ ሥላሴ ፍ.

ዲቨሎፐር እና UI/UX ዲዛይነር

ሃሳቦችን ወደ ውብ እና ተግባራዊ ምርቶች የመለወጥ አቅም አለኝ። እያንዳንዱ የደንበኛዎትን እይታ እንዲስብ እስከ ጥቃቅን ነገሮች ድረስ በኮድ እና በዲዛይን እዉን አደርጋለሁ።

TS

ታደለ ስ.

ውጥን(ፕሮጀክት) አስኪያጅ

ሀብተ ትኩረቱን እንዳይስት፣ በተደራጀ መልኩ እንዲሰራ እና እያንዳንዱን ፕሮጀክት በሰዓቱና ከተጠበቀው በላይ ጥራት ባለው መልኩ እንዲያስረክብ አደርጋለሁ።

ማስታወሻ፡ ልዩ የግራፊክስ ስራ ይፈልጋሉ? ፕሮጀክቶች ሲፈልጉ በኔትወርኬ ውስጥ ካሉ ጎበዝ ዲዛይነሮች ጋር አብሬ እሰራለሁ። ነገር ግን እርስዎ ሁልጊዜ ከእኔ ጋር በቀጥታ ይሰራሉ።

እኔን ተዋውቀዉናል፣ አሁን ደግሞ የእርስዎ ተራ ነው፡ እንተዋወቅ።

የሙያ ማረጋገጫዎች

ዘመናዊ የድር ቴክኖሎጂዎችን በማወቅ ያለኝን ቁርጠኝነት ማሳያ።

ማንኛውም የማረጋገጫ ማስፈንጠሪያ ከተበላሸ፣ እባክዎ ኢሜል ይላኩልኝ

The AI Engineer Path
Scrimba

The AI Engineer Path

IBM Frontend Developer
IBM

IBM Frontend Developer

Meta Frontend Developer
Meta

Meta Frontend Developer

The Frontend Developer Career Path
Scrimba

The Frontend Developer Career Path

JavaScript Deep Dive
Scrimba

JavaScript Deep Dive

Learn Responsive Web Design
Scrimba

Learn Responsive Web Design

Google UX Design
Google

Google UX Design

Learn UI Design
Scrimba

Learn UI Design

ሂደቶቸ

ከምርምር እና ከቅድመ ንድፍ ጀምሮ እስከ የሙከራ ንድፍ ድረስ፡ ቀላል የተጠቃሚ ተሞክሮዎችን እፈጥራለሁ።

01

ግኝት እና ምርምር

ስለ ንግድዎ፣ ግቦችዎ እና ተጠቃሚዎችዎ በመማር እንጀምራለን። በውይይት፣ በቃለ-መጠይቆች እና በምርምር አማካኝነት የዲዛይን አቅጣጫችንን የሚያሳውቁ ግንዛቤዎችን እንሰበስባለን።

Step 01ፍላጎቶችዎን መረዳት
02

መስተጋብሩን ማዋቀር

የተጠቃሚ አጠቃቀም ጉዞን እና የምርትዎን የመረጃ አወቃቀር ለመቅረጽ ቅድመ ንድፍን እሰራለሁ። ይህም ግልጽና ለአጠቃቀም ቀላል የሆነ ዲዛይንን ለማምጣት ያደርጋል።

Step 02ቅድመ ንድፍ
03

መልክ እና ስሜትን መፍጠር

ንድፍ አውጪዎቻችን ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ሞዴሎችን ያዘጋጃሉ፣ ይህም በሚያምር የተጠቃሚ ተሞክሮ ላይ በማተኮር በውበት፣ ከምርት ስምዎ ጋር የተመጣጠነ አሰላለፍ እና ተደራሽነት ላይ ያተኩራል።

Step 03የእይታ ንድፍ
04

ተሞክሮውን ማረጋገጥ

የሚያገለግሉ የሙከራ ንድፎችን ሰርተን እንጨርስና ከተጠቃሚዎች እና ከርስዎ አስተያየት እንሰበስባለን፣ ከዚያም ንድፉን እናሻሽላለን።

Step 04የሙከራ ንድፍ እና አስተያየት

የአገልግሎቶቼን ሂደት ወደዋቸዋል? ቀጣዩ ፕሮጀክትዎ ላይ ልረዳዎት ዝግጁ ነኝ::

እኔን ከሌሎች የሚለዩን ነገሮች

ለምን ደንበኞቻችን እኔን እንደሚመርጡ ይወቁ።

ግልጸኝነት

በፕሮጀክቶቼ ላይ ደንበኞቼ አጠቃላይ ሂደቱን እና በየትኛው የስራው ክፍል ላይ እንዳለሁ በግልጽ ያያሉ።

እንከን የለሽ ትብብር

በተደጋጋሚ ማሻሻያዎችን እና የአስተያየት ልውውጦችን በማድረግ ከደንበኞች ጋር በቅርበት እሰራለሁ።

በአመክንዮ ላይ የተመሰረቱ ስልቶች

የምከተላቸው ስልቶች ውጤታማ እና ዘላቂነት ያለውን ትብብር ለማረጋገጥ በጠንካራ አመክንዮ እና ምክንያት ላይ የሚገነቡ ናቸው።

ሊያድጉ የሚችሉ መፍትሄዎች

የምሰጣቸው መፍትሄዎች ከንግድዎ ፍላጎቶች ጋር እንዲያድጉ እና እንዲላመዱ የሚነደፉ ናቸው።

ብጁ መፍትሄዎች

ለእርስዎ ልዩ ፍላጎቶች የተዘጋጁ መፍትሄዎችንም አቀርባለሁ።

ፈጠራ ያለው ንድፍ

የእኔ የንድፍ አካሄድ የምርት ስምዎ ጎልቶ እንዲወጣ ያደርጋል።

ባለሙያነት

ልምድ ያለኝ እና ለልህቀት የቆምኩ ባለሙያ ነኝ።

አስተማማኝ ድጋፍ

ስኬታማ መሆንዎን ለማረጋገጥ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እሰጣለሁ።

ነፃ ምክክር

ደውሉልኝ ፡ ከዛም ምን እንደሚጠቅምዎት እና እንዳማይጠቅምዎት እወያያለሁ። በውይይታችን ላይ ምን ቢወስኑ እንደሚያዋጣዎት እና የእርስዎን ጥያቄዎች ብቻ እንመልሳለን እንጂ አገልግሎቶቼን ለመሸጥ ለማሳመን አልሞክርም። የ20 ደቂቃ ብቻ ውይይት።

ተደጋግመው የሚጠየቁ ጥያቄዎች

ስለአገልግሎቶቼ እና ሂደቶቸ ለሚነሱ የተለመዱ ጥያቄዎች መልሶችን ያግኙ።

የተጠቃሚ በይነገጽ እና ተሞክሮ ዲዛይን(UI/UX) እና የድረ ገጽ አገልግሎቶችን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቼ እሰራለሁ። ለተለዩ ፍላጎቶችዎ የተዘጋጁ አጠቃላይ የዲጂታል መፍትሄዎችን ለመፍጠር ቁርጠኛ ነኝ። ዝርዝር መረጃ ለማግኘት እባክዎ የአገልግሎቶቼን ገጽ ይጎብኙ።